Polly po-cket
free book gift

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።


Iqra

=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=

ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ


1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።

2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።

3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።

4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
Iqra
Iqra

Homeየወጣቱ ተልዕኮ ምንነትየአቂዳ ትምህርቶችየሶላት መመሪያረመዷንሙስሊም ሴቶችኢስላማዊ ቤተሰብከታሪክ ማህደርሐዲስለወጣቶችትምህርትና መሰረታዊ ክህሎታችጤናችንግጥምጥያቄና መልስኢስላማዊ መዝገበ ቃላት
free book gift

=<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=

ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ!

free book gift

በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

free book gift

የነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) የመጨረሻ ዳዕዋ(ጥሪ)


✍ በወጣቱ ተልዕኮ(አህመድ የሱፍ)
Iqra
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

ሰዎች ሆይ! ከዚህ አመት ቡኋላ በድጋሚ ከናንተ መካከል መሆኔን አላውቅምና ጆሮዋችሁን አውሱኝ። ስለዚህ የምነግራችሁን ነገር በደምብ አድምጡ፤ ንግግሬንም ዛሬ እዚህ ቦታ ላይ ለሌሉ ሰዎች አድርሱ።

ሰዎች ሆይ! እንደምታውቁት ይህ ወር ፣ ይህ ቀን እና ይች ከተማ የተቀደሱ ናቸው። እናም የእያንዳንዱ ሙስሊም ህይወት እና ሃብት ንብረት የተቀደሰ አደራ እንደሆነ እወቁ። በአደራ መልክ የተሰጣችሁን ሸቀጦች(ንብረቶች) ለባለቤቶቻቸው መልሱ። ማንንም አትጉዱ፤ ማንም አይጎዳችሁምና። በእርግጥም ጌታችሁን እንደምትገናኙ እና ስራዎቻችሁን እንደምትተሰሳቡ እወቁ። አሏህ አራጣ መብላትንም ከልክሏችኋል፤ ስለዚህ ሁሉም አራጣ ከእንግዲህ ወዲህ ሊቀር ይገባል።

ለሃይማኖታችሁ ደህንነት ሸይጧንን ተጠንቀቁ። ሊያጠማችሁ በሚችልባቸው ትልልቅ ነገሮች ላይ ተስፋ አጥቷልና በትንንሽ ነገሮች እሱን ከመከተል ተጠንቀቁ።

ሰዎች ሆይ! ሴቶቻችሁን በተመለከተ በእነሱ ላይ መብቶች ያላችሁ መሆኑ እውነት ነው። ነገር ግን እነሱም በናንተ ላይ መብቶች አሏቸው። መብታችሁን ከጠበቁ በደግነት የመመገብና የመልበስ መብት ይገባቸዋል። አጋሮቻችሁ እና እረዳቶቻችሁ ናቸውና በደምብ ተንከባከቧቸው፤ መልካም(ደግ) ሁኑላቸው። ካልፈቀዳችሁላቸው ጋር ጓደኞችን ላያበጁና ዝሙትን በፍፁም ላይፈፅሙ ይህ የእናንተ መብት ነው።

ሰዎች ሆይ! በቅንነት አዳምጡኝ። አሏህን ተገዙ ፣ አምስት አውቃ ሶላታችሁን ስገዱ ፣ በረመዷን ወርም ፁሙ ፣ ንብረታችሁንም በዘካ መልክ ስጡ ፣ የቻላችሁም ሐጅ አድርጉ።

እያንዳንዱ ሙስሊም ለሌላኛው ወንድም እንደሆነ ታውቀላችሁ። ሁላችሁም እኩል ናችሁ። ማናችሁም በሌላው ላይ በላጭነት የለውም በተቅዋውና በመልካም ስራው ብቻ ቢሆን እንጅ።

አስታውሱ! አንድ ቀን ከአሏህ ፊት ቀርባችሁ ለስራዎቻችሁ መልስ ትሰጣላችሁ። እናም ካረፍኩ(ከሞትኩ) በኋላ ከቀጥተኛው መንገድ መጥመምን ተጠንቀቁ።

ሰዎች ሆይ! ከእኔ በኋላ ነብይ አይመጣም፤ አዲስ እምነትም አይፈጠርም። በደንብ አስቡ! ሰዎች ሆይ! ያስተላለፍኩላችሁን ንግግሬን ተረዱ። ከኋላየ ሁለት ነገሮችን ትቸላችኋለሁ (ቁርአን እና ሱናን) እነሱን አጥብቃችሁ እስከያዛችሁ ድረስ አትጠሙም።

እኔን ያደመጡ ሁሉ ንግግሬን ያስተላልፉ፤ እንዲሁም ሌሎች ለሌሎችም። የመጨረሻዎቹ ሰዎችም ንግግሬን በቀጥታ ካደመጡ ሰዎች በላይ በተሻለ የተረዱ(የተገነዘቡ) ሰዎች ይሁኑ። አሏህ ሆይ! ምስክሬ ሁን ለህዝቦችህ መልዕክትህን አድርሻለሁ። {በማለት ነበር የመጨረሻ ዳዕዋቸውን ያደረጉት}

469

የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
free book gift

Download Islamic Books
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ

Important Web Links


free book gift

free book gift

free book gift

ስለወጣቱ ተልዕኮ ምንነት ለማወቅ እዚህ ላይ ክሊክ ያድርጉ

Copyright©Youth-Mission የወጣቱ ተልዕኮ